Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ800 እና 1 ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደሚቀጥለው ዙር አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሽቱን በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በተካሄደው የወንዶች 800 ሜትር እና የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደሚቀጥለው ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በዚሁ መሰረት÷ አትሌት ኤርሚያስ ግርማ 1 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ ከ39 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት እንዲሁም አትሌት መርሲሞይ ካሳሁን 1 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባትወደሚቀጥለው ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል።
ምሽቱን በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች የማጣሪያ ውድድር ደግሞ ÷ አትሌት መብርሂት መኮንን 4 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ከ97 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 1ኛ በወውጣት ወደሚቀጥለው የፍፃሜ ውድድር አልፍለች።
እንዲሁም አትሌት ብርቄ ኃየሎም 4 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ከ6 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ወደሚቀጥለው የፍፃሜ ውድድር አልፋለች ።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version