Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሻሸመኔ ከተማ ህገ ወጥ የውጭ ሀገር ገንዘብ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ የውጭ ሀገር ገንዘብ ተያዘ።
ገንዘቡ ከአዲስ አበባ ወደ ሞያሌ በሚጓዝ የጭነት ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ መያዙን የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ምክትል ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር አብዱልጀባር ዑስማን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።
የተያዘው ገንዘብ 77 ሺህ 665 ዩሮ እና 11 ሺህ 110 ፓውንድ መሆኑንም ተናግረዋል።
ይህም በብር ሲተመን 4 ሚሊየን 868 ሺህ 262 ብር ከ57 ሳንቲም መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በጌታቸው ሙለታ
Exit mobile version