Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኬንያ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት ዊሊያም ሩቶ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኬንያ 5ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት ዊሊያም ሩቶ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ።

በኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዊሊያም ሩቶ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋን በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።

ይህንን ተከትሎ የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስተላለፉት የደስታ መግለጫ፥ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት መልካም እድልን ተመኝተዋል።

የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ነው ያረጋገጡት።

Exit mobile version