Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች እንዲጠናከሩ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የተጀመሩ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎች በሁሉም ቢሮዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ጤና እና ውኃና ኢነርጂ ቢሮዎች በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝታቸውም÷ በክረምቱ ወቅት የአቅመ ደካማዎችን ቤት በማደስ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በማከናወንና በጎ ሥራዎችን በመሥራት ቢሮዎች የጀመሩትን መልካም ተግባር እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።
የበጎ ፈቃድ ሥራ የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት ኖሮት አቅመ ደካሞችን በሁሉም መስክ ማገዝ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ማስገንዘባቸውን የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version