Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ እና አውስትራሊያን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ አምባሳደር ፀጋዓብ ከበበው ገለጹ 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና አውስትራሊያ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ፀጋዓብ ከበበው ተናገሩ።

አምባሳደር ፀጋዓብ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውስትራሊያ አስተዳደር ጄኔራል አቅርበዋል።

አምባሳደር ፀጋዓብ በዚሁ ወቅት ከአስተዳደር ጄኔራሉ ጋር መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይታቸውም የሀገራቱን የረጅም ዘመን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር፣ በመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣትና ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ተግተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

 

Exit mobile version