Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም በጅማና ወላይታ ሶዶ ከተሞች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮ ቴሌኮም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በጅማ እና በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በጅማ ለሚገኙ 3 ሺህ 999 እና በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ለሚገኙ 200 አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ነው የተደረገው፡፡

በአጠቃላይ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ለሚገኙ 800 ተማሪዎች ድጋፉ እንደሚደረግ ኢትዮ-ቴሌኮም ገልጿል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ 55 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የደብተር ድጋፍ ማድረግ አንዱ መርሐ-ግብሩ እንደሆነና በሀገር ደረጃ 726 ሺህ 800 ደብተሮችን ለመለገስ ማቀዱም ተገልጿል፡፡

በሀገር ደረጃ ድጋፉን እያደረገ ያለውም “አብሮነት ለነገ ተሥፋችን”በሚል መርኅ ነው፡፡

በመለሰ ታደለ እና ተመሥገን አለባቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version