Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በወልዲያ ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ መርሐ- ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደም ልገሳ መርሐ- ግብር በወልዲያ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የደም ልገሳው በጦር ግንባሮች የኢትዮጵያን ክብር ለማስጠበቅ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር እየተፋለመ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በወልዲያ ከተማ እየተካሄደ ያለውን የደም ልገሳ መርሐ ግብር ያዘጋጀው በሰሜን ወሎ ዞን የጉባ ላፍቶ ወረዳ ከወልዲያ የደም ባንክ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር መሆኑም ነው የተገለጸው።

የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች በግንባር ለሚገኙ የጦር ሠራዊት አባላት ደጀንነታቸውን ለማሳየት እና አጋርነታቸውን ለመግለጽ ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version