Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

21ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 21ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ጥናት ጉባኤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡

 

በጉባኤው ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሪሾ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃናን ጨምሮ ሌሎች ምሁራን፣ተመራማሪዎችና እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

 

ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ጉባኤው “‘የኢትዮጵያ ጥናት ዓለም አቀፋዊ እና ብሔራዊ አውድ፣ተግዳሮትና ጽናት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

 

በጉባኤው በኢትዮጵያ የተካሄዱ ጥናቶችን በሚመለከት በተለያዩ ምሁራን ጽሁፍ ቀርቦ ምክክር ከተደረገ በኋላ የቀጣይ ምልከታ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Exit mobile version