Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የድሬዳዋ ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ከ500 በላይ ሠልጣኞች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ከ500 በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ።

ኮሌጁ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ፣ በማፋክቸሪንግ ፣ በሆቴል ሥራ አመራር፣ በድራፍቲንግና ሰርቬይንግ በተለያዩ ደረጃዎች እስከ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 543 ሠልጣኞች ነው ያስመረቀው።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሐር ባስተላለፉት መልዕክት፥ ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ሥራ በመሥራት ለሀገራቸው ብልፅግና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።

በተለይም በቅርቡ ይፋ የተደረገው የድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለሚመረቁ ተማሪዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ስላለው ተመራቂዎች ዕድሉን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ጥሪ አስተላልፈዋል።

የድሬዳዋ ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ÷ ሀገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ-መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የምታደርገው ጥረት ኮሌጁ ገበያው የሚፈልገውን የተማረ እና በዕውቀትና ክኅሎት የዳበረ የሰው ኃይል በማቅረብ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኮሌጁ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 297ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በመቅደስ ደረጃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version