አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወላይታ ዞን ለመከላከያ ሠራዊት ከ 34 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉም÷ 116 ሰንጋዎችና እና 387 በግና ፍየሎችን እንዲሁም የተለያዩ ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን ያካተተ ሲሆን÷ በአጠቃለይ 17 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት እንዳለው ተገልጿል፡፡
ከተደረገው የዓይነት ድጋፍ በተጨማሪ 17 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ የስልጤ ዞን ማኅበረሰብ ለመከላከያ ሠራዊት ከ13 ሚሊየን በላይ ብር ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
እንዲሁም የጎፋ ዞን ሴቶች አደረጃጀቶች ለመከላከያ ሠራዊት 3 ሚሊየን 685 ሺህ ብር ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ አድረገዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!