Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከችልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከችልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ኬት ሀምፕተን ጋር በጤናው ዘርፍ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ዶክተር ሊያ ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን የማህበረሰቡን ጤና ከመጠበቅ አኳያ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ችልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን የጤናውን ዘርፍ በመደገፍ ረገድ ላልተቋረጠ ድጋፉና ትብብሩም ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version