Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ፡፡

ልዑኩ ገራድ ዊል ዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በሌሎች የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የሶማሌ ክልል፥ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተናግዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version