Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘው ሳንሼንግ ፋርማቲካል በቀን 24 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘር ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዱከም የሚገኘው ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘው ሳንሼንግ ፋርማቲካል በቀን 24 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘር ማምረት ጀመረ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ አበባየሁ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘው ሳንሼንግ ፋርማቲካል የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ማምረት ላይ ትኩረት የሚያደርግ አዲስ ክፍል መክፈቱን ገልፀዋል።

አዲሱ ሳንሼንግ ፋርማቲካል የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ማምረቻ በቀን ውስጥ 24 ሺህ ሊትር ማምረት የሚችል መሆኑንም አስታውቀዋል።

ፋብሪካው ትኩረቱን የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ላይ አድርጎ መስራቱም በሀገር ውስጥ ያለውን ፍላጎት ለመሙላት ያግዛል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ አበበ አበባየሁ።

 

Exit mobile version