Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚዘክርና የሰላም ስምምነቱን የሚደግፍ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን የግፍ ጭፍጨፋ ሁለተኛ ዓመት የሚዘክርና በፌዴራል መንግስትና በሕወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።

“በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ መቼም አንረሳውም”፣ የተደረገውን ስምምነት እንደግፋለንና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመከባበርና በፍቅር መኖር አለበት” የሚሉ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ እየተላለፉ ይገኛሉ።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የሰላም ስምምነቱ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባውም ሰልፈኞቹ በያዟቸው መልዕክቶች መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version