Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት 8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀምሯል።

በንግድ ትርዒቱ የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የአልባሣት፣ የቤት ማሥዋቢያ፣የቴክኖሎጂ እንዲሁም ኢንዱስትሪ ምርቶችና ፈጠራዎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

የንግድ ትርዒቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ማህበር ከመሴ ፍራንክፈርት ግሩፕ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት፡፡

ከ30 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒቱ÷አምራቹን በዓለም ዙሪያ ካሉ በርካታ የንግድ ባለሙያዎች እና ግብዓት አቅራቢዎች ጋር እንደሚያገናኝ ታምኖበታል።

የንግድ ትርዒቱ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚቆይ መሆኑንም ተመላክቷል፡፡

በታሪኩ ለገሰ እና በሰሎሞን ይታየው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version