አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ዛሬ ቀን 10 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን በይገዙ ቦጋለ ሁለት ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በባህርዳር ደካማ ጊዜን ያሳለፈው ሲዳማ ቡና ስዩም ከበደን የቡድኑ አሰልጣኝ ካደረገ ወዲህ ሁለት ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና አዲስ አዳጊውን ለገጣፎ ለገዳዲን ተመስገን ብርሃኑ በባከነ ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ጥሩ አጀማመር እያሳየ ያለው ሀድያ ሆሳዕና ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡