Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

50 የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አመራሮች ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለገሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች የተለያዩ አካላት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል ድጋፍ ማድረጋቸው እንደቀጠለ ነው።
 
50 የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አመራሮች ትናንት ባደረጉት ስብሰባም የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት እንዲውል የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል።
 
የብልፅግና ፓርቲ በቅርቡ ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ካሰባሰበው ገንዘብ ውስጥ 100 ሚሊየን ብር ቫይረሱን ለመከላከል እንዲውል ለግሷል።
 
ገንዘቡ በመላው ሀገሪቱ የንፅህና መጠበቂያ መግዛት ለማይችሉ ዜጎች እንደሚውል ተመልክቷል።
Exit mobile version