Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከባንግላዴሽ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከባንግላዴሽ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይቱ በኢትዮጵያ በፀሐይ ሃይል፣ በሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ያሳዩ የባንግላዴሽ ባለሃብቶች ተሳትፈዋል፡፡
 
አምባሳደር ናዝሩል የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን በማስተዋወቅ የባንግላዴሽ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ እየሠሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲዳብር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውንም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ባለሀብቶቹ በፕሮጀክታቸው ይዘት ላይ ለኮሚሽነሯ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን÷ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version