Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢንሳ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የከተማ አስተዳደሩን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና ለማዘመን “አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ የማድረግ” የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ያለመ ነው ተብሏል።

አሰራሩም ከተማዋን በማዘመን የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንስና ከተማዋ ያላትን ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚመጥን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል እንደሚሆን ይጠበቃል መባሉን የከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version