አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል የምትሳተፍበትን ጨምሮ አራት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡
በዚህም በምድብ ሁለት የተደለደሉት ዌልስ ከኢራን ቀትር 7 ሰዓት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን ÷ በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት እንግሊዝ ከአሜሪካ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ አንድ የሚገኙት የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ኳታር ከአፍሪካዊቷ ሴኔጋል ቀን 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡
በዚሁ ምድብ የሚገኙት ኔዘርላንድስ ከኢኳዶር ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያካናውኑ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡
ቀደም ብሎ በተካሔደው የመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ አሜሪካ ከዌልስ 1 አቻ ሲለያዩ÷ ኔዘርላንድስ ሴኔጋልን 2 ለ 0፣ እንግሊዝ ኢራንን 6 ለ2 እንዲሁም ኢኳዶር ኳታርን 2 ለ0 ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!