Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለሚጠቀሙ የንግድ ተቋማት ድጋፍ ታደርጋለች – ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በሀገር ውስጥ የበለጸጉ የመረጃ እና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለሚጠቀሙ የንግድ ተቋማት ድጋፍ የምታደርግ መሆኑን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ፡፡

ድጋፉ ግብር በመቀነስና እና ማበረታቻዎችን በመፍቀድ ይተገበራልም ነው የተባለው፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎ ጉባዔ በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በጉባዔው የተሳተፉ ሲሆን ÷ በዘርፉ ሀገራቸው መሻሻሎችን እንድታስመዘግብ ለመደገፍ ተጨማሪ ገንዘብ የመመደብ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በ“ክላውድ ቴክኖሎጂ” ላይ የሚሠሩ የሀገሪቷ አምራች ኩባንያዎች ድጋፍ እንዲያገኙ መመሪያ ማስተላለፋቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

ሀገራቸው በፕሮጀክት ደረጃ አቅዳ በሰው ሰራሽ አስተውሎ ላይ እንደምትሠራም ነው ፕሬዚዳንት ፑቲን ያስታወቁት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version