Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል ኳታርን 3ለ1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ የምድብ 2 የሁለተኛ ዙር ጨዋታ  አፍሪካዊቷ ሴኔጋል  አዘጋጇን ሀገር ኳታር  3 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

በኳታር አልቱማም ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡሊያን ዲያ፣ ፋሙራ ዴዴሁ እና ባባ ዲየንግ  የሴነጋልን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ሞሃመድ ሞንታሪ የኳታርን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

የቴራንጋ አንበሶቹ በኔዘርላንድስ ከደረሰባቸው ሽንፈት በማገገም ከምድቡ ለማለፍ  እና በኳታር ለመቆየት የሚያስችላቸውን ድል አስመዘግበዋል፡፡

የአፍሪካ ሻምፒዮኖቹ በመጀመሪያው ዙር የአለም ዋንጫ ጨዋታ በመጫረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩባቸው ጎሎች በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 ተሸንፈው እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

 

 

Exit mobile version