Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ነቢል ማሃዲ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የደህንነት አማካሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲድ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት የደህንነት አማካሪ ቱት ጋትሉዋክ ጋር ተወያዩ።

በዚህ ወቅትም አምባሳደር ነቢል ለአማካሪው በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረሰው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት የደህንነት አማካሪ ቱት ጋትሉዋክ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን አወንታዊ ተነሳሽነት አድንቀዋል።

አያይዘውም በኢትዮጵያ ያለው ሰላም በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ላይ መሰረታዊ ተፅዕኖ እንዳለው መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በውይይታቸው ወቅት የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

Exit mobile version