Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ስዊድን የሕግ ታራሚዎችን ለማረምና ለማነጽ የሚደረገውን ጥረት እንድምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድን የህግ ታራሚዎችን አርሞ እና አንጾ ለማውጣት እንዲሁም በማሰልጠኛ ተቋሙ ብቁ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተደረገ ያለውን ጥረት አንደምትደግፍ ገልጻለች፡፡

በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄነሪ በአሌሊቱ ከተማ የሚገኘውን በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የማረሚያ ፖሊስ ማሰልኛ ተቋምን እና የሴቶች ማረሚያ እና ማረፊያ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

አምባሳደሩ በማእከሉ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙርያ የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው የሚያስችል ገለጻ እንደተደረገላቸው ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ሃንስ በሁለቱም ማዕከላት እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የስዊድን መንግስት የህግ ታራሚዎችን አርሞ እና አንጾ ለማውጣት እንዲሁም በማሰልጠኛ ተቋሙ ብቁ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተደረገ ላለው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version