Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢ/ር ታከለ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ግንዛቤ ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ከተማ መጨናነቅ በሚታይባቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረጉ ጥንቃቄዎች ዙሪያ ምልከታ አድርገዋል።

በዚህ መሰረትም በመርካቶ፣ አትክልት ተራና መገናኛ አካባቢዎች መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች በተለይም በሰዎች መካከል መጠበቅ ስላለባቸው ርቀቶች ግንዛቤ መስጠታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version