Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በትምህርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በትምህርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የደቡብ ሱዳን የከፍተኛ ትምህርት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጋብርኤል ቻንግሰን ቻንግ የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የምትሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል ለማሳደግ ያስችላል።

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትምህርት ዘርፍ የቆየ ትብብርና ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክረውም መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የደቡብ ሱዳን የከፍተኛ ትምህርት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጋብርኤል ቻንግሰን ቻንግ በበኩላቸው÷ ሰነዱ ሁለቱ ሀገራት በትምህርት መስክ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሰው ጠቁመዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሱዳን የኢትዮጵያ ኮሙኒቲን ያነጋገሩ ሲሆን፥ ከኮሙኒቲው የተበረከተ 6 ሺህ የ7 እና 8ኛ ክፍል አጋዥ መጻህፍትን ተቀብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሚሰጠው ነጻ የትምህርት እድል በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን የነጻ ትምህርት ተጠቃሚ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Exit mobile version