Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለአማራ ክልል 600 የውሃ ፓምፖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 600 የውሃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የተደረገው በክልሉ የሚገኙ የመስኖ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ ዛሬ የተካሄደው የሁለትዮሽ የምክክር መድረክ በተጠናቀቀበት ወቅት መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የውሃ መሳቢያ ፖምፖቹን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ያስረከቡት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ ናቸው።

ርዕሰ መስተዳድሩም ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው የውሃ ፓምፖቹ በፍትሃዊነት እንደሚከፋፈሉና ለታሰበላቸው ዓላማ እንደሚውሉ አረጋግጠዋል።

 

 

Exit mobile version