Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ሱዳን በህዳሴ ግድብና በድንበር ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማሙ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሱዳን በህዳሴ ግድብ እና በድንበር ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እና ባቋቋሟቸው የሁለትዮሽ የትብበር መድረኮች በኩል ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ ጋር በሱዳን ካርቱም ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያና ሱዳን በህዳሴ ግድብ እና በድንበር ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እና ባቋቋሟቸው የሁለትዮሽ የትብበር መድረኮች በኩል ለመፍታት መስማማታቸውም ተገልጿል፡፡

ጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ ÷ ሱዳን በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version