Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጋና በአለም ዋንጫው ሁለተኛ የአፍሪካ ተሰናባች ሀገር ሆናለች

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም ዋንጫው የምድብ ማጣሪያ ጋና በኡራጋይ ተሸንፋ ከምድብ ተሰናብታለች፡፡

በጨዋታው ጋና በ2010 የዓለም ዋንጫ ከሩብ ፍፃሜ ያሰናበተቻትን ኡራጋይ ትበቀላለች ቢባልም በኳታሩ አልጃኑብ ስታዲየም ታሪክ ራሱን ደግሟል፡፡

በደቡብ አፍሪካው የአለም ዋንጫ አሳሞሃ ጅያን ፍፁም ቅጣት ምት ስቶ ጋና በመለያ ምት የተሸነፈች ሲሆን በዛሬው ጨዋታም አንድሬይ አዩ ፍፁም ቅጣት ምት ስቶ ጋና በኡራጋይ 2 ለ 0 ተሸንፋለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሶከር-ሲቲ ስታዲየም አፍሪካዊያንን ያበሳጨ የእግርኳስ ምሽት ዛሬም በኳታሩ አልጃኑብ ስታዲየም ተደግሞ የአፍሪካ ኮከቦችን ከምድብ አሰናብቷል፡፡

በምድቡ ደቡብ ኮሪያ ከፖርቱጋል ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ያንግ ጎውን ለደቡብ ኮሪያ እንዲሁም ሪካርዶ ሆርታ ለፖርቹጋል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተክትሎም ከምድብ 8 ፓርቹጋል እና ኡራጋይ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል፡፡

Exit mobile version