አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት አማኖ በሪሶ እና ለተሰንበት ግደይ በስፔን ቫሌንሲያ ማራቶን ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በስፔኑ የዛሬው የቫሌንሲያ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አማኖ በሪሶ ርቀቱን በ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመጨረስ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባ አሸንፋለች።
አትሌት ለተሰንበት ግደይ ደግሞ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ በመግባት የራሷን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ውድድሩን ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡
በወንዶች የቫለንሲያ ማራቶን ኢትዮጵያ ከሜዳያ ውጭ ስትሆን÷ ኬንያዊው ኬልቪን ኬፕቱን ወድድሩን በቀዳሚነት አሸንፏል፡፡