Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

8ኛው የኢትዮ- ሩሲያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ሩሲያ 8ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ነገ ከሕዳር 27 ቀን እስከ ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የሚኒስትሮቹ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በትምህርት እንዲሁም በንግድ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራል።

ነገ ለሚጀመረው ስብሰባም የሩሲያ ልዑካን በዛሬው ዕለት  አዲስ አበባ መግባታቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ልዑካኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር  በለጠ ሞላ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Exit mobile version