Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር መንገዱ በውጭ ሀገር ለሚታከሙ 100 የልብ ሕሙማን የትራንስፖርት ወጪ ሊሸፍን ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ100 የልብ ሕሙማን ሕጻናት ቀዶ ጥገና ወደሚያደርጉበት ሀገር ደርሰው የሚመለሱበትን ሙሉ የትራንስፖርት ወጪ እንደሚሸፍን አስታወቀ፡፡

በዛሬው ዕለትም አየር መንገዱ ለመጀመሪያ አራት ተጓዦች ሽኝት አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ በሽኝቱ ላይ እንደተናገሩት÷ ሕጻናትን ማዳን ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡

በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይም የህንድ አምባሳደር እና የሮተሪ ኢትዮጵያ ቺፍ ኦፊሰር ተገኝተዋል፡፡

በውጭ ሀገር የሚታከሙትን ሕጻናት የቆይታ እና የሕክምና ወጪ ደግሞ ሮተሪ ኢትዮጵያ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡

በትዕግስት አስማማው

Exit mobile version