Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮሚቴው ተጨማሪ 16 ተሽከርካሪ የህክምና ግብዓቶችን በትግራይ ክልል እያሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ተጨማሪ16 ተሽከሪካሪ ምግብ እና የህክምና ግብዓቶች በትግራይ ክልል በሚገኙ ሆስፒታሎች እያሰራጨ መሆኑን አስታውቋል፡፡
 
ኮሚቴው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ ÷የሰብዓዊ እርዳታ ምግብ እና የህክምና ግብዓቶችን የጫኑ 16 ተሽከርካሪዎች ትናንት ሽረ ከተማ መግባታቸውን ገልጿል፡፡
 
የሰብዓዊ እርዳታ ግብዓቶቹ በክልሉ ለሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች መሰራጨት መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡
 
ግብዓቶቹ ለታማሚዎች እና ለጤና ተቋማት ባለሙያዎች የሚከፋፈሉ መሆኑንም ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የህክምና ግበዓቶችን ወደ ገጠራማ አካባቢዎች የማሰራጨት ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡
Exit mobile version