Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሣምንት ጨዋታ የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

የኢትዮ ኤሌክትሪክን ጎሎች ኢብራሂም ከድር በ60ኛው እንዲሁም ናትናኤል ሰለሞን በ74ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

የአርባምንጭ ከተማን ጎሎች ደግሞ አሕመድ ሁሴን በ3ኛው እና አላዛር መምሩ በ95ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችለዋል፡፡

በሌላ የ11ኛ ሣምንት የጨዋታ መርሐግብር መቻል ሳሙኤል ሳሊሶ በ74ኛው እና በረከት ደስታ በ89ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሐዋሳ ከተማን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡

Exit mobile version