Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ሕዳር 29፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከአውሮፓ ሕብረት የቢዝነስ ፎረም ጋር በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

እንዲሁም ከአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገራት መሳብ ስለሚቻለው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡

እንዲሁም መድረኩ በኢትዮጵያ መዋዕለነዋያቸውን አፍስሰው በመሥራት ላይ ለሚገኙ የአውሮፓ ኩባንያዎች እየተደረገ ስለሚገኘው ድጋፍ እና ክትትል ላይ እየመከረ መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮምሽነር ለሊሴ ነሜ እና የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮናልድ ኮቢያ በውይይ ላይ እንደገለጹትት÷ ይህን መሰል የምክክር መድረኮች የአውሮፓ ሕብረትን እና የኮሚሽኑን ግንኙነት ለማጠናከር ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡

Exit mobile version