Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

4ኛው የጀርመን-አፍሪካ የቢዝነስ ጉባዔ በጆሃንስበርግ እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛው የጀርመን- አፍሪካ የቢሰዝነስ ጉባዔ 2022 በጆሃንስበርግ እየተካሔደ ነው፡፡
በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የጀርመን ምክትል ቻንስለርና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስትር ሮበርት ሃቤክ÷ የጀርመን መንግሥት በአፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ለማበረታታት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር በጉባዔው ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ከጉባዔው ጎን ለጎንም ከተለያዩ ሀገራት የሥራ ኃላፊዎችና የንግድ ማህበረሰብ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስር መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version