Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለሲዳማ ክልል 300 የውኃ መሳቢያ ፓምፓችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለበጋ ስንዴ ልማት የሚያግዙ 300 የውኃ መሳቢያ ፓምፓችን ለሲዳማ ክልል ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢኒጂነር አይሻ መሐመድ ለሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስረክበዋል፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ ዘንድሮ ከ10 ሺህ ሔክታር በላይ በመስኖ እየለማ መሆኑን ጠቁመው÷ ሚኒስቴሩ በክልሉ እየተከናወኑ ለሚገኙ የመስኖ ሥራዎች እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

በክልሉ በጊዳቦ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን የመስኖ ፕሮጀክት ወደሥራ ለማስገባት ከሚኒስቴሩ ጋር በቅንጅት እየሠራን ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በድጋፍ እርክክቡ ላይ ኢንጂነር አይሻ እንደገለጹት÷ ክልሉ ዘንድሮ እያከናወነ ለሚገኘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የውኃ መሳቢያ ፓምፓቹ ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ፡፡

 

Exit mobile version