Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር በጅማ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛኦ ዚያን በጅማ ከተማ በቻይና መንግስት ድጋፍ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
 
አምባሳደር ዛኦ ዚያን በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከልየሚደረጉ ትብብሮች የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት የሚያሳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
ጅማ ታሪካዊ ከተማ መሆኗን ያነሱት አምባሳደሩ ÷ የቻይና መንግስት በቀጣይ በኢትዮጵያ ብሎም በጅማ ከተማ የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
 
አምባሳደር ዛኦ ዚያን በጂማ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጉብኝት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጀማል አባፊጣ ጋር ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
Exit mobile version