Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ( ባባ ) የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ( ባባ ) የቀብር ፅነ ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡

ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ታሪኩ ብርሃኑ ባደረበት ህመም ምክንያት ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን፥ ሥርዓተ ቀብሩ በዛሬው ዕለት የአርቲስቱ ቤተሰቦች ፣ ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከ40 በላይ በሚሆኑ ፊልሞች በመሪ ተዋናይነት እና በተዋናይነት ተሳትፏል፡፡

አርቲስቱ ከተሳተፈባቸው ፊልሞች መካከል ላውንደሪ ቦይ፣ 300 ሺህ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ፣ ኢንጂነሮቹ፣ ህይወቴ፣ ከቃል በላይ፣ ህይወትና ሳቅ፣ ሀገርሽ ሀገሬ፣ እዮሪካ፣ ከባድ ሚዛን፣ ወፌ ቆመች፣ በቁም ካፈቀርሽኝ፣ እንደ ቀልድ፣ እርቅ ይሁን፣ ሞኙ ያራዳ ልጅ 4፣ አባት ሀገር እና ወጣት በ97 በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበር።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በድጋሚ መጽናናትን ይመኛል።

Exit mobile version