Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጓዥ አንባቢዎች “የ2022 ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ዘርፍ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሜሪካው “ግሎባል ትራቭለርስ” መፅሔት ከመንገደኞች በሚያሰባስበው ድምፅ መሰረት በሚያበረክተው የእውቅና ሽልማት “የ2022 ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” አሸነፈ፡፡

“ግሎባል ትራቭለርስ” 19ኛውን ዓመታዊ የተጓዥ አንባቢ አሸናፊዎች የእውቅና ሽልማት መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በዚሁ መመሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የሞሮኮው ሮያል ኤር ማሮክ እና የኬኒያ አየር መንገድ በአፍሪካ ምርጥ አየር መንገዶች ሆነው መመረጣቸውን የ“ግሎባል ትራቭለርስ”  መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

Exit mobile version