Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባንኩ ከ11 ሺህ በላይ ሰራተኞችን በመቅጠር ሒደት ላይ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ11 ሺህ በላይ ሰራተኞችን በመቅጠር ሒደት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፈተናውን ሒደት አስመልከቶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በዛሬው ዕለት የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ባንኩ የቅጥር ሒደቱ ፍጹም ታዓማኒ እንዲሆን የጽሑፍ ፈተናውን የአዲስ አበባ የኒቨርሲት የንግድ ክፍል እንዲሰጥ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
 
የባንኩ የሰው ሃይል አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ÷ ፈተናውን ለመፈተን ከ130 ሺህ በላይ ዜጎች አመልክተው መስፈርቱን የሚያማሉ ተመዝጋቢዎች በሙሉ ፈተና መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
 
ባንኩ ባለፉት አራት ተከታታይ እሑዶች የጽሑፍ ፈተና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ሲሰጥ ቆይቶ መጠናቀቁንም አንስተዋል፡፡
 
በማህበራዊ ትስስር ገጾች ፈተናው ወጥቷል ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን የገለጹት አቶ ኤፍሬም ÷የጽሑፍ ፈተናውን በኮድ ከማድረግ ጀምሮ አስፈላጊ ጥንቃቄ መደረጉን ጠቁመዋል።
 
በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ የንግድ ስራዎች ስራ ትምህርት ክፍል ሃላፊ ዶክተር አብራራው ጫኔ በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን ከማዘጋጀት ጀምሮ እስከ ውጤት ድረስ በጥንቃቄ ማከናወኑን ገልጸዋል።
 
ዩኒቨርሲቲው ከፈተናው ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠመው እና በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲሰራጭ የነበርው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በቅድስት ብርሃኑ
Exit mobile version