Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል ለማቅረብ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡

በተቋሙ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ እንደገለጹት÷ መንግሥት በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ የጀመረውን ጥረት ለማገዝ እየተሠራ ነው፡፡

በዚህም ለተሽከርካሪዎቹ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ዕቅድ እንደተዘጋጀ መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመላክታል።

ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው÷ ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል፡፡

Exit mobile version