Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለበጋ መስኖ ስንዴ ውጤታማነት አማራጮችን በመጠቀም እየተሠራ መሆኑን አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ውጤታማነት ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

በአቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ ልዑክ በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ዳቡስ ቀበሌ በ35 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር እየለማ የሚገኝ የበጋ መስኖ ስንዴ ማሳን ጎብኝቷል።

በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በታቀደው ልክ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም መሥራት እንደሚገባ አቶ አሻድሊ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ መንግስት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ለማሳካት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

 

 

 

Exit mobile version