Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሌ ክልል ዲጎዲያ ጎሳ መሪ ወበር አብዲሌ ወበር አብዲ የኬንያን የሰላም የክብር ሽልማት ተቀበሉ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ዲጎዲያ ጎሳ መሪ ወበር አብዲሌ ወበር አብዲ የኬንያን የሰላም የክብር ሽልማት ተቀበሉ።

ሽልማቱን የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ወበር አብዲሌ ወበር አብዲ በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አበርክተውላቸዋል።

የሰላም የክብር ሜዳሊያው የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የቀድሞው በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ አለም እና የሃገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ተበርክቶላቸዋል።

በቆንጅት ዘውዴ

Exit mobile version