Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)25ኛው የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣አባ ገዳዎች፣ ሀዳ ሲንቄዎችና ከህብረተሰቡ የተውጣጡ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ጉባኤው “ለተሳካ ትምህርት የሚመለከታቸው አካላት እና የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ ወሳኝ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ እንደሚገኝ ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ጉባኤው ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም የክልሉን የመማር ማስተማር ሂደት በተመለከት የተከናወኑ ተግባራ ላይ ይመክራልም ነው የተባለው፡፡

Exit mobile version