Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባሌ ሮቤ-ጎሮ-ሶፍ ኡመር-ጊኒር መገንጠያ መንገድ ግንባታ የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሌ ሮቤ-ጎሮ-ሶፍ ኡመር-ጊኒር የመንገድ መጋጠሚያ ማሻሻያ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
 
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የከተማና መሰረተ ልማት ሚስትር ጫልቱ ሳኒ እና የኦሮሚያ ክለል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና ፌዴራል የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
የመንገድ ፕሮጀክቱ 120 ነጥብ 65 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ÷ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንደሚገነባ መገለጹን ከርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version