Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ልማት ለማሻሻል ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን እና ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን የሆሃ ቁጥር-10 የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ለአምባሳደሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን÷ ስለክልሉ የልማት እንቅስቃሴዎችም ገለጻ አድርገዋል።
 
በኢትዮጵያ ቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን በበኩላቸው÷የቻይና መንግስት የክልሉን ልማት ለማሻሻል ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸው ÷ በተለይም የትምህርት ዘርፍ ስራ ውጤታማ እንዲሆን ያግዛል ብለዋል።
 
አምባሳደሩ ለሆሃ ቁጥር -10 ትምሀርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version