Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ታይቶበት ህይወቱ ያለፈው የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮና ቫይረስ እንደነበረበትና እንዳልነበረበት እየተጣራ ነው- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ህክምና ሲደረግለት የነበረ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ ዛሬ ህይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ከሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ትናንት ወደ ጤና ጣቢያ ለህክምና ያመራው ግለሰቡ ዛሬ ህይወቱ ማለፉንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ግንኙነት እንዳለውና እንደሌለው ለማረጋጋጥ ናሙና ተወስዶ የምርመራ ውጤቱ እየተጠበቀ መሆኑንም አብራርተዋል።

የአስከሬን ምርመራም እየተከናወነ መሆኑን ጨምረው መግለፃቸውን ነው ኢዜአ የዘገበው።

Exit mobile version