Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩ 80 ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ግጭት በደረሰ የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ውድመት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩ 80 ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
 
በግጭቱ ምክንያት ኤሌክትሪክ ተቋርጠባቸው የነበሩ የትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልል አካባቢዎችን ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ በተደረገ ከፍተኛ ጥረት 80 ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
 
ቀሪ 27 ከተሞችን መልሶ ለማገናኘት የጥገና ስራ እየተከናወነ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
 
ተቋሙ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ጦርነት በኤሌክትሪክ ማሰራጫ መሠረተ-ልማቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት ከስር ከስር መልሶ በመጠገን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች ዳግም ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
Exit mobile version