Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታና ነባሩን በአዲስ የማደራጀት ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታና ነባሩን በአዲስ የማደራጀት ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመድረኩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ፣ የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኩታዬ ኩስያ፣ የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ የዞንና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡
 
አሁን ላይ የፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ የአንድ ወር የዕቅድ አፈጻጸም በዓብይ አስተባባሪ ኮሚቴው እየተገመገመ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version